የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኃይማኖት አባቶች የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማዋ ለተሰሩ ግዙፍ የልማት ስራዎች ምስጋና አቀረቡ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኃይማኖት አባቶች የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማዋ ለተሰሩ ግዙፍ የልማት ስራዎች ምስጋና አቀረቡ

AMN – ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት እና በከተማዋ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ሀሳብ ያመነጩ እና ስራ ላይ ያዋሉ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የኮሪደር ልማት እና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ከተጎበኙ ልማቶች መካከል የአራት ኪሎ ፕላዛ ፣ የገላን ጉራ የመኖሪያ መንደር ፣ ብርሃን የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት እና የለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ይገኙበታል፡፡

በጎብኝቱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ስራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ እና የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዋና ፀሀፊ አቡነ ዲዮስቆሮስን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል፡፡

በከተማዋ የተሰሩት የልማት ስረዎች ለሕዝብ እና ለሀገር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው እና በበለጸጉ ሀገራት የሚታይ የልማት ስራ በሀገራችን መስራት እንደሚቻል ማሳያ ነውም ብለዋል ሊቃነ ጳጳሳትና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላቱ፡፡

በጎብኝቱ በከተማዋ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረጉ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን መታዘብ ችለናል ነው ያሉት፡፡

በአዲስ አበበ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች ለትውልድ የሚሻገሩ እና በመላ ሀገሪቱ መስፋፋት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ይህም በቀጣይት የሀገርን ገፅታ ለመቀየር ጥሩ መነሻ በመሆኑ ሕዝቡ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review