AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
የ2026 የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ከካሜሩን አቻው ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 ተሸንፏል።
የካሜሩንን የማሸነፊያ ብቸኛ ግብ ታዛኑ አንጌ በ12ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፋለች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ከካሜሩን የተሻለ እንቅስቃሴ በማሳየት ብልጫ ቢወስድም ያገኛቸውን ዕድሎች ባለመጠቀሙ ለሽንፈት ተዳርጓል ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ጨዋታ በአጠቃላይ 6ለ2 በመሸነፍ ማጣሪያውን ሳያልፍ ቀርቷል።
በአዲሱ መንገሻ