የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዛሬ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዛሬ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዛሬ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አሸንፏል፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲዬም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በተካሄደው በሁለቱ የመዲናዋ ክለቦች በኢቲዮ-ኤሌክትሪክና በኢትዮጵያ ቡና መካከል በተደረገው ጨዋታ፣ በኢትዮጵያ ቡና 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ኮንኮኒ ሀፊዝ ከእረፍት በፊት ከመረብ ያሳረፋት ብቸኛ ግብ ኢትዮጵያ ቡናን ባለ ድል አድርጋለች፡፡ ማሸነፉን ተከትሎ ኢትዮጲያ ቡና በ32 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢቲዮ- ኤሌክትሪክ በ 25 ነጥብ 10ኛ ላይ ይገኛል፡፡

ምሽት 12፡00 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከሀዲያ ሆሳዕና ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 ሲጠናቀቅ፣ መስፍን ታፈሰ ለሲዳማ ቡና፣ እዮብ አለማየሁ ለሀድያ ሆሳዕና ግቦችን ከመረብ ያሳረፉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና በ32 ነጥብ 3ኛ ሲሆን ሲዳማ ቡና በ25 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ነገ ስሁል ሽረ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀለ 70 እንደርታ ከሃዋሳ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

በኦብሴኔት ክፍሌ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review