
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሃግብር ዛሬ በሚከናወኑ ሁለት ጨዋታዎች ፍፃሜውን ያገኛል።
9 ሰዓት ላይ ባህርዳር ከተማ ከመቻል ይጫወታሉ። ባህርዳር ከተማ በሂሳባዊ ስሌት ከዋንጫ ፉክክር አልወጣም።
ዛሬ ድል ከቀናው ነጥቡን 50 ያደርሳል። ከመሪው ኢትዮጵያ መድን የሚነሮው የነጥብ ልዩነትም ወደ 10 ዝቅ ይላል።
ባለፈው ዓመት በአንድ ነጥብ ተበልጦ ዋንጫ ያጣው መቻል ዘንድሮ ያን ብቃቱን መድገም ተስኖታል። አሁን ላይ ከመድን በ19 ነጥብ አንሶ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዲያ ሆሳዕና ከ ስሁል ሽረ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በ41ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ሀዲያ የተሻለ ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ ስሁል ሽረ ላለመውረድ ጨዋታው ያስፈልጋቸዋል።
በ21 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ስሁል ሽረ ዛሬ ካላሸነፈ ወልዋል አዲግራት ዩኒቨርስቲን ተከትሎ የመውረድ እድሉ በእጅጉ ይሰፋል።
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሃዋሳ ቆይታውን ዛሬ ያገባድዳል።ቀጣይ ቀሪ የስድስት ሳምንት መርሃግብሮችን በአዳማ የሚያከናውን ይሆናል።