የኢትዮ – እስራኤል የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ

You are currently viewing የኢትዮ – እስራኤል የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ

AMN- ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከእስራኤል አቻቸው ጌዲዮን ሳር ጋር በመሆን ”በፈጠራ ሥራዎች የሁለቲዮሹን ግንኙነት ማጠናከር ”በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮ-እስራኤል የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ከፍተዋል።

ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ታሪካዊ መሠረት ያለው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁን ላይ በግብርና፣ በውኃ አስተዳደር፣ በጤና፣ በመከላከያ፣ በቴክኖሎጂ እና ትምህርት ዘርፎች እየተጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።

የዛሬው የቢዝነስ ፎረም ግንኙነቱን በኢኮኖሚ ዘርፍ የበለጠ በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ እስራኤል በሰውሰራሽ አስተውሎት እና ተያያዥ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከፍተኛ አቅም ያላት በመሆኑ ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ በትብብር ትሰራለች ብለዋል።

ሚኒስትሩ የእስራኤል ጎብኝዎች በኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የእስራኤሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት በብዙ መስኮች የተጋመደ መሆኑን በመግለጽ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

የእስራኤል ኩባንያዎች እና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም መዋዕለ ንዋያቸውን እንደሚያፈሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በቢዝነስ ፎረሙ የንግድ ኩባንያዎች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መታደማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review