
AMN – ጥር 3/2017 ዓ.ም
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ የቅዳሜና እሁድ የስልጠና መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
ስልጠናው በይፋ የተጀመረው ኢመደአ በ2016 ዓም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ያሰለጠናቸዉን 237 ተማሪዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡
ስልጠናው በተቋሙ የሳይበር ልሕቀት ማዕከል ውስጥ የሚሰጥ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም በአዲስ አበባ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ስልጠናውን ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ምቹ ሁኔታ (የስልጠና ቦታ፣ ኮምፒውተር እና የኢንተርኔት አቅርቦት) በነጻ እንዲያገኙና ስልጠናውን በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ስልጠናውን ለመውሰድ ከ8ሺ በላይ ሰልጣኞች መመዝገባቸውን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
