የኢኮኖሚ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት እንሰራለን-የልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች

You are currently viewing የኢኮኖሚ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት እንሰራለን-የልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች

AMN – መጋቢት 7/2017 ዓ.ም

የኢኮኖሚ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚሰሩ በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት የልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች ተናገሩ።

የከተማ ግብርና ላይ ስፋት ለመስራት የሚያስችል የሴፍቲኔት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

እንደ ከተማ ከ154 ሺ በላይ ዜጎች በፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን፤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ደግሞ ከ14 ሺ 3መቶ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።

በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተፈፀመ የሚገኘው የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ድጋፍ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ዘላቂ ገቢ ለማሳደግ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

እንደ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከመደገፍ ባለፈ ዘላቂ የስራ እድል እንዲፈጠር የተለያዩ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት አራት ዋና አላማዎች እንዳሉት ተነግሯል። ዛሬ የተመረቁት ዜጎች 12 በሚደርሱ በተለያዩ መስፈርቶች ተመዝነው ያለፉ ስለመሆናቸው ተገልጿል።

ህብረተሰቡ ካለበት ኢኮኖሚያዊ ችግር በዘላቂነት እንዲላቀቅ በሴፍቲኔት ፕሮግራም እየተሰራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፤ የከተማ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የሆኑ ስራዎችን በማከናወን በሴፍቲኔት ፕሮግራም ከ154 ሺ በላይ ዜጎች ድጋፍ እና ቋሚ የስራ እድል አመቻችቷል።

በዛሬው እለትም የከተማ ግብርና ላይ ስፋት ለመስራት የሚያስችል የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጀምሯል።

በዚህም የስራ እድሉ የተፈጠረላቸው ዜጎች ድጋፍን በዘላቂነት ለመፍታት መትጋት እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review