AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሰላም እና ደህንነት አስተባባሪ ቡድን በአዲስ አበባ ስብስባውን እያደረገ ይገኛል።
የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ስብስባውን አስጀምረዋል።

በስብሰባው ላይ የኢጋድ የሰላም እና ደህንነት ፕሮግራም ዳይሬክተሮች፣ ልዩ ልዑኮች እና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።
የቡድኑ ስብስባ ኢጋድ በፈረንጆቹ 2025 እና በ2026 በሰላም እና ደህንነት ዘርፍ የቅድሚያ ትኩረት የሰጣቸውን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ከአጋር አካላት ፍላጎቶች ጋር አጣጥሞ ማስኬድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል።
የትብብር ማዕቀፉ ኢጋድ ለቀጣናው መረጋጋት፣ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል እና የዲፕሎማሲ መፍትሄዎችን ገቢራዊ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።