
AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም
በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ ኅዳር 22 የሚከበረውን አለም አቀፍ የኤች አይቪ ኤድስ ቀንን አስመልክቶ የጤና ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ 36ኛ ጊዜ ኅዳር 22 ይከበራል።
ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጄ ድጉማ (ዶ/ር) የኤች አይቪ ኤድስ የማህበረሰባችን ችግር ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።
የኤች አይቪ ኤድስ በተለይ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት ጤና ሚኒስቴር እየሰራ መሆኑንና በዚህም ስርጭቱን በመቀነስ ረገድ ውጤት መታየቱን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው አሁንም አሳሳቢ በሽታ መሆኑን አስታውቀዋል።
በበሽታው የተጠቃ ሰዎች ላይ አድሎ መገለል ና እንዳይኖር በማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል።
ማህበረሰቡም እራሱን በመጠበቅ እራሱን ሊከላከል ይገባል ተብሏል።
በመሀመድ ኑር አሊ