
በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሃግብር ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይከናወናሉ፡፡ ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ስታዲየም ቦርንማውዝን ያስተናግዳል፡፡
የውድድር ዓመታቸውን ያለዋንጫ የሚያጠናቅቁት ሲቲዎች ታላቁ ተጫዋቻቸውን ኬቨን ደብሩየናን ይሸኛሉ፡፡ ቤልጄማዊ አማካይ 10 ዓመት ካሳለፈበት ክለብ የሚመጥነውን ሽኝት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማንችስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላሱ የኤፍ ኤ ዋንጫ ፍፃሜ ሽንፈት ስብራት ለመጠገን የዛሬው ድል ያስፈልገዋል፡፡ በቀጣይ የውድድር ዓመት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎአቸውን ለማረጋገጥም ማሸነፍ ግዴታ ይሆንባቸዋል፡፡ በ65 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ድሉ ወደ ሦስተኛ ከፍ ያደርገዋል፡፡

ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍ ኤ ዋንጫን ያነሳው ክሪስታል ፓላስ ወልቭስን ያስተናግዳል፡፡ ለሁለቱም ክለቦች የተሸለ ደረጃ ይዞ ለመጨረስ ካልሆነ ጨዋታው ትልቅ ትርጉም የለውም፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ