የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምሥራቅ ባሌ ዞን የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

AMN – ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልል እና የፌዴራል አመራሮች የልዑካን ቡድን በምሥራቅ ባሌ ዞን በለገ ሂዳ ወረዳ በክላስተር እየለማ የሚገኝ የማሽላ እና የጤፍ ምርት እየጎበኘ ነው።

በዞኑ በክረምት ዝናብ ከ508 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በተለያዩ የእህል ዓይነቶች ለምቷል።

በዞኑ የሚገኙ ቆላማ አርብቶ አደር ወረዳዎች ከዝናብ ጠባቂነት ተላቅቆ ዝናብ እና መስኖ በመጠቀም የተለያዩ የሰብል አይነቶችን በማልማት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር ላይ ይገኛሉ።

በባሌ ዞን ከሚገኙ ቆላማ ወረዳዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ለገ ሂዳ ወረዳ በአሁኑ ወቅት 54 ሺህ ሔክታር የሚሆነው መሬት በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች ተሸፍኗል።

በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የልዑካን ቡድን የምሥራቅ ባሌ በመገኘት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኘ መሆኑን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review