በጉባኤው በኦሮሞ ባህል ፣ ቋንቋ ፣ እሴትና አርት ላይ የተከናወኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።
ትውልዱ እሴቱንና ባህሉን በሚገባ እንዲያውቅ በማስቻል የጋራ ትርክት ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ፤ መደላድልን ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ መሆኑን የኦሮሞ ጥናትና ምርምር ኢኒስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ አስራት በተለይ ለ ኤ ኤም ኤን ተናግረዋል።
ባለፉት ስርአቶች ውስጥ ከአንድነት ይልቅ የሚለያዩ ነገሮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሰራ መቆየቱ በህዝቦች መካከከል አንዳንድ መገፋፈቶች እንዲከሰቱ ሆነዋል ፤ ያሉት አቶ ዝናቡ አሁን ግን ከሚለያዩን ይልቅ አንድ የሚያደርጉን እሴቶች ላይ በጥናትና ምርምር የተደገፈ ስራ በመስራት የህዝቦችን ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
መድረኩ ነገም ቀጥሎ የሚካሔድ ሲሆን አባ ገዳዎች ፣ ሐደ ሲንቄዎች ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣ ሙሁራን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሔኖክ ዘነበና ሰላማዊት ተስፋዬ