የከተማችን ሰላምና ደኅንነት ከምን ጊዜውም በላይ በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው-የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

You are currently viewing የከተማችን ሰላምና ደኅንነት ከምን ጊዜውም በላይ በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው-የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

AMN-ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም

የከተማችን ሰላምና ደኅንነት ከምን ጊዜውም በላይ በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው ሲል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

ተቋሙን አስመልክቶ በአንዳንድ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወረውን የተዛባ መልዕክት መመልከቱን የገለፀው ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ አንዳች የፀጥታ ችግር ያለ ለማስመሰል የተደረገውን ጥረትም አስተውለናል ነው ያለው።

ይሁን እንጂ እስከአሁን ባደረገው ማጣራት መልዕክቱ በተቋሙ እንዳልተላለፈ እና ተቋሙን የማይወክል መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ ጉዳዩን የበለጠ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል።

የተላለፈው መልዕክትም ፍፁም ከከተማዋ ነባራዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር የማይገናኝ መሆኑን የገለፀ ሲሆን አሁን ላይ የመዲናዋ ሰላምና ደኅንነት ከምን ጊዜውም በላይ በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ እንዳለ በማኀበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review