የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የሁለተኛ ዙር የስራ እድልና የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ’’የከተማ ግብርና ለምግብ ዋስትና’’ በሚል መሪ ሀሳብ የማጠናከሪያ መርሀግብር ተካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ዉድነትን ለመቀነስ መስራት ብቻ ለችግሩ መፍተሄ እንደሆነ በማመን በዘረፉ ዉጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገልፀዋል፡፡
በተለይም ማህበረሰቡ የምግብ ዋስትናነዉን ከጓሮ እንዲያረጋግጥና ከተማዋ ላይ በቂ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል አርሷ አደሩንና ማህበረሰቡን የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡
በሚቀጥሉት 90 ቀናትም በከተማዋ የሌማትና የከተማ ግብርና ስራዉ ላይ ማህበረሰቡን በንቅናቄ ለማሳተፍ ስራዎች መጠናቀቃቸዉን አንስተዋል፡፡
የለሚ ኩራ ክፈለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ 64 በመቶ የከተማዋ አርሶ አደር የሚገኘዉ በክፍለ ከተማዉ ስር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሃላፊው አቅም ለሌላቸዉ ዜጎችን የስራ እድል ለመፍጠር በሌማት እና በከተማ ግብርና ዘርፍ የስራ እድል ተፈጥሯልም ብለዋል፡፡
በዚህም ክፍለ ከተማዉ ከ189 ሚሊየን ብር በላይ የፈጀ 5460 የዶሮ ኬጅ ከ140ሺህ በላይ ቄብ ዶሮዎችንና ሌሎች ግብአቶችን ከሁሉም ወረዳዎች ለተዉጣጡ አቅመ ደካማ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
በሩዝሊን መሃመድ