የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቀናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቀናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ሚያዝያ 21/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የከተማ አስተዳደራችንን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቀናል ብለዋል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀማችን አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ፣ ጽዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የቱሪስት መተላለፊያ ብቻ ሳትሆን መዳረሻ የሆነች ከተማ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር እንዲሁም የአመራር ቁርጠኝነትንና ቅንጅትን በማጠናከር የጀመርናቸው ሁሉን አቀፍ ስራዎችን በፍጥነት ጀምረን በመጨረስ ለዘጠኝ ወራት ያቀድናቸዉን ስራዎች በአማካይ 93% አሳክተናል ብለዋል፡፡

የነዋሪውን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ሌሎች ሰው ተኮር ስራዎቻችን የበርካቶችን ሸክም ያቃለሉ፣ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ ያበሱ እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ያረጋገጡ ሲሆኑ የፕሮጀክት አፈፃፀም፣ የገቢ አሰባሰብ፣የኑሮ ዉድነትን እና ገበያን የማረጋጋታ ስራ ፣የሰላምና ጸጥታ፣ የትራንስፓርት መሰረተ ልማት ማስፋፋት፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የበጀታችንን 71 % ለዘላቂ ልማት እና ደህነት ቅነሳ ማዋላችን፣ የስራ ባህል እየተሻሻለ መምጣቱ ዋና ዋና ውጤት ካገኘንባቸው ተግባራት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው::

ፈተናዎችን እየተሻገርን ባሳካናቸው ስኬቶች ሳንረካ ጥንካሬዎቻችንን በማጽናት በግምገማችን የለየናቸውን ድክመቶች ከነመንስዔዎቻቸው ነቅሰን በማውጣት እና ለላቀ ውጤታማ ስራ በመዘጋጀት በአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል፣ ኑሮ ውድነትን በመቀነስ፣ ቀሪ ኮሪደሮችን፣ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ እንዲሁም ሌብነትና ብልሹ አሰራር በማስቀረት ለነዋሪዎቻችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን ቀጥለናል::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review