AMN- ጥር 12/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ በተካሄደው የከተራና የጥምቀት በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳያጋጥም ተከብሮ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮሚሽን መ/ቤቱ በዓሉ ያለአደጋ ክስተት ተከብሮ እንዲያልፍ ከሀይማኖት አባቶችና ከበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር በመሆን ህብተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተገንዝቦ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል።
በዚህም በዓሉ ያለምንም አደጋ ክስተት ተከብሮ ማለፉን ነው ከኮሚሽን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።
ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግና የጥንቃቄ መልዕክቶች በማስተላለፍ ህብረተሰቡና የሚዲያ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል።
በበዓላት ጊዜ የተደረጉ የጥንቃቄ ተግባሮች በመደበኛና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችም ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።