AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም
የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪያ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር አብርሃም መንግሥቱ እና በሚኒስቴሩ የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ዶ/ር አዚዛ ገለታ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።