የኩዌት ፈንድ ለኢትዮጵያ ለልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

You are currently viewing የኩዌት ፈንድ ለኢትዮጵያ ለልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

AMN- ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም

የኩዌት ፈንድ የመሰረተ ልማት ግንባታ እና የልማት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታወቀ።

የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ መካሄዱን ቀጥሏል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኩዌት ፈንድ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዋሊድ አል-ባሃር ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ለዳይሬክተር ጀነራሉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የልማት ትኩረቶች እና የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ጅምር ውጤቶችን አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

የኩዌት ፈንድ መሰረተ ልማትን ጨምሮ ለተመረጡ ፕሮጀክቶች ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የኩዌት ፈንድ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዋሊድ አል-ባሃር በበኩላቸው፣ ፈንዱ የኢትዮጵያን ቁልፍ የመሰረተ ልማት እና ወሳኝ የልማት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው የኢትዮጵያ እና ኩዌትን አጋርነት ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሚያዚያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ ነገ ይጠናቀቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review