የኪነ ጥበብ ባለሙያው ለከተማዋ ልማት ቀጣይነት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing የኪነ ጥበብ ባለሙያው ለከተማዋ ልማት ቀጣይነት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለፀ

AMN-ግንቦት 30/2017 ዓ.ም

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝት መርሃግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) በመዲናዋ ሰፋፊ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀው ለልማቱ ቀጣይነት የኪነ ጥበብ ባለሙያው ሚና የላቀ እንደሆነም ተናግረዋል።

የጉብኝት መርሀግብሩ በካዛንችስ የተሰሩ የልማት ስራዎችን በመመልከት የተጀመረ ሲሆን የመዲናዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሆኑባቸው የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ ከሚመለከተው አካል ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉት ባለሙያዎች የልማት ስራው የዜጎችን ህይወት የለወጠ ስለመሆኑ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከጉብኝቱ መጠናቀቅ በኋላ ባለሙያዎቹ በአድዋ ሙዚየም ከከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review