የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ያደረገ እና ሰው ተኮር መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው ተባለ

You are currently viewing የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ያደረገ እና ሰው ተኮር መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው ተባለ

AMN – ሚያዝያ 30/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬትና የግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት እያከናወናቸው ያሉ የኮሪደር እና ሌሎች የልማት ፕሮጀክት ስራዎችን ገምግሞ ግብረ መልስ ሰጥቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ጃራ ሰማ፣ የኮሪደር ልማቱ “አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን” ተብሎ ለህዝቡ ከተገባው ቃል የመነጨ እና ሰው ተኮር መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ኃ/ማርያም በበኩላቸው፣ የህዝባችንን ፍላጎት መሰረት በማድረግ መቅደም ያለበትን የልማት ስራ አስቀድመን በከተማችን በ2ኛው ዙር 8 የኮሪደር ሳይቶች እና ኘሮጀክቶቸን 7/24 በመሥራት በጥራትና በላቀ አፈፃፀም እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል፡፡

የቢሮ ሀላፊዋ አያይዘውም፣ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት የመንገድ መሰረተ ልማት እና የአረንጓዴ ሽፋን እጅግ ከፍ ያለበት፣ የእግረኛና የሳይክል መንገዶች የተስፋፉበት፣ የህዝቡ ድጋፍና ትብብር የጨመረበት፣ ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል የተፈጠረበት መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ፣ የከተማው ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከያዘው ተልዕኮ አንፃር የሚያከናውናቸው ተግባራት ከጊዜ ወደጊዜ በውጤት የታጀበ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ቢሮው የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለመከታተልና ለመቆጣጠር እንዲችል የራሱ የሆነ ሶፍትዌር እንዲኖረው እና የሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት መጠቆሙን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review