የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ

You are currently viewing የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ

AMN ግንቦት – 26/2017ዓም

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል ገለጹ፡፡

በክፍለ ከተማው “የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ ከሁሉም ወረዳዎች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር የማጠቃለያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል እንደገለጹት፣ ወጣቶች ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ብልጽግና መዳበር ትልቁን ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡

መንግሥት ለወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡

የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ቱኩ በበኩላቸው፣ ወጣቶችን ቀጣይነት ባላቸው የሥራ ዘርፎች በማሰማራት ተጠቃሚ ለማድረግ ከሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ጋር በጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ወጣቶችን በስፖርት፣ በበጎ ፈቃድ ሥራዎች እና በሌሎችም የአካልና የአእምሮ ብቃትን በሚያጎለብቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲሳተፉ ይስራል ያሉት ደግሞ የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም ናቸው፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው፣ ሀገራችን በምታደርገው የልማት እንቅስቃሴ በመሳተፍ የድርሻችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review