የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ሱዳን በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገለፀ

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ሱዳን በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገለፀ

AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገልጿል።

በግዛቱ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ20 መንገደኞች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል።

ሚኒስቴሩ ለደቡብ ሱዳን ህዝብ እና መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።

በዚህ ከባድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ደቡብ ሱዳን መንግሥት እና ሕዝብ ጎን በመሆን ያለውን አጋርነትም ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review