የዓለማችን ቁጥር አንድ የዕድሜ ባለጸጋዋ መነኩሲት በ116 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ሲስተር ኢና ካናባሮ ሉካስ በፈረንጆቹ ሰኔ 8 ቀን 1908 በደቡባዊ ብራዚል ሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል ግዛት ነበር የተወለዱት።
በ20ዎቹ ዕድሜያቸው መጀመሪያ ወደ ምንኩስና የገቡት ሲስተር ኢና ካናባሮ የእግር ኳስ ቀንደኛ አፍቃሪ እንደነበሩም ይነገራል።
መነኩሲቷ ሁሌም ልደታቸውን የሚያከብሩት በሚወዱት የሀገራቸው ክለብ ኢንተርናሽናል ፖርቶ አሌግሬስ ስታዲየም ቅርፅ የተሰራ ኬክ በመቁረስ እንደነበረም ቤተሰቦቻቸው አውስተዋል።
ሲስተር ኢና ካናባሮ ከዚህ ቀደም ስለረጅም ዕድሜያቸው ምስጢር ተጠይቀው ሲመልሱ፣ “የህይወት ምስጢር ፈጣሪ ነው” ብለው ነበር።
እግር ኳስ አፍቃሪዋ መነኩሲት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ፣ የ115 ዓመቷ እንግሊዛዊት ኢቴል ካተርሃም የዓለም የዕድሜ ባለጸጋ ክብረ ወሰንን መረከባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል