የዓለም ሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ በግንቦት ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል

You are currently viewing የዓለም ሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ በግንቦት ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል

AMN- ህዳር 5/2017 ዓ.ም

20ኛው የዓለም ሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ ከግንቦት 11 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ. ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ጉባኤውን አስመልክተው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ጉባኤው ከግንቦት 11 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል ብለዋል።

“በአስቸጋሪ ዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታን መቋቋም የሚችል ማህበረሰብ መፍጠር” በሚል መሪ ሃሳብ ጉባኤው እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በጉባኤው የኮንስትራክሽንና የመሰረተ ልማት ድርጅቶች የሚሳተፉ በመሆኑ ለስራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።

በጉባኤው የዘርፉን ዕድሎችና ፈተናዎች የሚዳስሱ ጥናታዊ ጹሁፎች እንደሚቀርቡም አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ተሳታፊዎቹ በኢትዮጵያ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ተናግረዋል።

በጉባዔው ፖሊሲ አውጪዎች፣ የአሰሪዎች እና የሰራተኞች ማህበራት እና ሰራተኛ-ተኮር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የአካዳሚክ እና የምርምር ተቋማት እንደሚሳተፉ ጠቅሰዋል።

ጉባኤውን በስኬት ለማከናወን ከ15 የመንግሥት ተቋማት የተወጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑ ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review