የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትን የማሳካት ጉዳይና ሂደቱ የሃገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲከናወን የጠራ አቋም ይዘናል-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

You are currently viewing የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትን የማሳካት ጉዳይና ሂደቱ የሃገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲከናወን የጠራ አቋም ይዘናል-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

AMN – የካቲት 22/2017 ዓ.ም

ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት እ.አ.አ ማርች 19 ቀን 2025 ለሚደረገው 5ኛ ዙር የሥራ ቡድን ስብሰባ በየቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ላለፉት ሶስት ቀናት ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ከትናንት ጀምሮ የብሔራዊ ተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት የቴክኒክ ኮሚቴውን ዝግጅት ሥራ በቢሾፍቱ በመገምገም ላይ እንደሚገኙ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የድርድሩን ባህሪና ውስብስብነትን ያገናዘበ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ የጠራ አቋም መያዝ የሚያስችል ጥልቅ ውይይት በማድረግ ላይ እንገኛለንም ብለዋል፡፡

በድርድሩ ምላሽ በሚሰጥባቸው ጉዳዮች በተለይ ከንግድና ንግድ ነክ ሕጎች፣ ለንግድ ተግዳሮት ሊሆኑ የሚችሉ ቴክኒካል ጉዳዮች፣ ስታንደርድ፣ የወጪ ንግድ ፈቃድ፣ ከኢንቨስትመንት ማዕቀፍ፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደርና አሠራር፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና አስተዳደር ጉዳዮች፣ ከግብር ጋር የሚያያዙ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎች እና በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትን የማሳካት ጉዳይና ሂደቱ የሃገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲከናወን የጠራ አቋም ይዘናል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review