AMN-መጋቢት 12/2017 ዓ.ም
የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 800 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል።
20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በቻይና ናንጂንግ ተጀምሯል።
የሴቶች 800 ሜትር ውድድር የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል።
ከምድብ 1 የተሳተፈቺው አትሌት ሀብታም አለም በ2:04:48 ሰዓት ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ፣
አትሌት ፅጌ ዱግማ ከምድብ 2፣ በ2:04:52 ሰዓት አንደኛ ደረጃ፣ አትሌት ንግስት ጌታቸው ከምድብ 3 በ2:03:91 ሰዓት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ፣ ሶስቱም አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል።
ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት በሁለቱም ፆታ 1500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።
በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7:33 ላይ የሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ እና 8:18 ላይ የወንዶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድሮች የሚካሄዱ መሆኑን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።