የዓለም ጤና ድርጅት የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ስምምነትን አፀደቀ

AMN ግንቦት 12/2017 ዓ.ም

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ለወረርሽኞች ዓለም አቀፍ ዝግጁነትን ማሻሻል ያስችላል የተባለ ስምምነትን አጽድቋል።

ከሦስት ዓመታት ድርድር በኋላ የፀደቀውን ስምምነት 124 ሃገራት ሲደግፉት ፤ ፖላንድ፣ሩሲያ እና እስራኤልን ጨምሮ 11 ሀገራት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፤ ስምምነቱ ዓለምን ከወደፊት ወረርሽኝ በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ ያስችላል ብለዋል።

ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ምላሽ ለመስጠት የነበረው ክፍተት በተለይ ለድሃ ሀገራት የክትባት፣ የህክምና እና የምርመራ ፍትሃዊ ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይዘነጋም።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review