የዓድዋ ድል ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መወለድ መሰረት ጥሏል ፡-የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ

You are currently viewing የዓድዋ ድል ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መወለድ መሰረት ጥሏል ፡-የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ

AMN- የካቲት 9/2017 ዓ.ም

በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ የዓድዋ ድል ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መወለድ መሰረት መጣሉን አስታወቁ ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሯ የዓድዋን ድል በተለይ ለአፍሪካውያን የሚያጭረውን ሥሜት አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ በንግግራቸው የዓድዋ ድል የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎችን ቅስም የሰበረ፣ ለአፍሪካዊያን እና ትውልደ አፍሪካዊያን ብርሓንን የፈነጠቀ መሆኑን አመልክተዋል ፡፡

መልካምነት ፤ ክፋትን እንደሚያሸንፍ ብርሃንም፤ ጨለማን እንደሚገፍ እና ይህንንም እውን ለማድረግ አፍሪካዊያን በአንድነት ተባብረው ሲቆሙ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አስገንዝበዋል፡፡

እንደ ፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝነታቸው የተገነዘብቡት ፤ የፓን አፍሪካኒዘም እንቅስቃሴ የተወለደው በዓድዋ ድል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አፍሪካውያን ገት ጎዳና መገስገስ እንዲችሉ የፖለቲካ ነፃነታቸውን ማግኘት ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ የካሪቢያን ልጆች ከአፍሪካውያን ወንድሞች እና እህቶቻቸው ጋር አንድነታቸውን የማጠናከር ጽኑ ህልም እና ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

የዓድዋ ድል ፓን አፍሪካኒዝምን የፈጠረ እና የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ኣፍሪካውያን ለነፃነት ያደረጉትን ትግል የወለደ እና የቅኝ ገዢዎችን እቅድ እና ምኞት መና ያስቀረ እንቅስቃሴ እንደነበርም ጠቅላይ ሚኒስትሯ አስታውሰዋል፡፡

የህዝቦቻችንን መፃኢ እድል የተሻለ ማድረግ ዛሬ በእኛ እጅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰተሯ፣ የዓድዋ ጀግኖችን ድል መድገም ይጠበቅብናል ብለዋል።

በወርቅነህ አብዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review