
AMN- ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከተመረቀ ዕለት ጀምሮ ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፍፈረንሶችን በማስተናገድ ከተማችንን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት “ከረሃብ ነጻ ዓለም” ጉባኤ በከተማችን በአድዋ ድል መታሰቢያ በጥሩ ሁኔታ ተካሂዶ ተጠናቋል ብለዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከተመረቀ ዕለት ጀምሮ የዚህ አይነት ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፍፈረንሶችን በማስተናገድ ከተማችንን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል ሲሉም አመለክተዋል።

አዲስ አበባን የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እንዲሁም የስበት ማዕከል ለማድረግ የሰራናቸው ስራዎች ፍሬ አፍርተው ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ኮንፍራንሶችን ማስተናገድ በመጀመራችን ደስተኞች ነን ሲሉ ገልጸዋል።
በርትተን ስንሰራ ብዙ እጥፍ መልሶ እንደሚከፍለን ይህ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
እነዚህ ኮንፈረንሶች በከተማችን እንዲካሄዱ ያቀዳችሁ፣ የሰራችሁ እና ያስተናገዳችሁ አካላትን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁም ብለዋል።