የዓድዋ ድል እና የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአብሮነት ያሳኳቸው ዘመን ተሻጋሪ ድሎች ናቸው – ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)

You are currently viewing የዓድዋ ድል እና የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአብሮነት ያሳኳቸው ዘመን ተሻጋሪ ድሎች ናቸው – ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)

AMN- የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የዓድዋ ድል እና የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በየዘመናቸው በአብሮነት ያሳኳቸው ዘመን ተሻጋሪ ድሎች ናቸው ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለፁ።

ህዳሴ ግድቡ ኢትዮጵያውያን አንድነትን፣ የአይቻልም አስተሳሰብን በማሸነፍ በተግባር ያረጋገጡበት ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ትልቅ ታሪክ ነው ብለዋል።

መላው ኢትዮጵያዊያን በጋራ ርብርብ ያገባደዱት የዘመኑ አሻራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የዓድዋ ድልም ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው የጸረ ቅኝ ግዛት ትግል በማድረግ ለመላው የዓለም ጥቁር ህዝቦች ጭምር ኩራት የሆነ ዘመን ተሻጋሪ ድል እንደሆነ አንስተዋል።

የህዳሴ ግድብን እና የዓድዋ ድልን በርካታ የሚያመሳስላቸው ነገሮች እንዳሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ዓድዋ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ወኔ፣ ጀግንነት እና ህብረ ብሔራዊ አንድነት የተጎናጸፉት ድል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም ኢትዮጵያውያን በራሳቸው የፋይናንስ አቅም አንድነታቸውን በማጠናከር ያሳኩት ዘመን ተሻጋሪ ድል አድራጊነትን ያሳዩበት ነው ብለዋል።

የዓድዋ ድል የውጫሌ ስምምነትንና ቀኝ ገዥዎች በጥቁር ህዝቦች ላይ የነበራቸውን ያልተገባ አስተሳሰብ ያሸነፈ መሆኑን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ህዳሴ ግድብም በአባይ ወንዝ ላይ ያዘጋጁትን ሰነዶች በትብብር ማዕቀፍ ስምምነት እና የህዳሴ ግድብን በመገንባት ዳግም ድል የተጎናፀፍንበት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review