የዘመኑ ዐርበኝነት ድህነትና ኋላቀርነትን ቀርፎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing የዘመኑ ዐርበኝነት ድህነትና ኋላቀርነትን ቀርፎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

AMN – ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም

የዘመኑ ዐርበኝነት ድህነትንና ኋላቀርነትን ቀርፎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላፉት መልዕክ፣ ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን የማንነታችን መገለጫ እና የጀግንነታችን ማሳያ በሆነው “የዐርበኞች (የድል) ቀን”፣ 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የጥናትና ምርምር ውድድር መድረክን አስጀምረናል ብለዋል፡፡

የክህሎት ልማት ለሀገራችን ዕድገት እና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን በማመን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሰራናቸው ስራዎች በፈጠራ የበሰሉ ብሩህ አዕምሮዎችን፣ የተፍታቱ እጆችን፣ በክህሎታቸው የበቁ ዜጎችን ለማፍራት አስችለዋል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን፡፡

ኢትዮጵያ ወራሪ ጠላትን መክተው ሉዓላዊነቷን ያስጠበቁ ጀግኖች ዐርበኞች እንደነበሯት ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ የሙያንና የክህሎትን አቅም በመጠቀም ግብርናችንን የሚያዘምኑ፣ ለኢንዱስትሪ ዕድገት ወሳኝ መነሻ የሆኑ፣ የቱሪዝም ዘርፉን ውጤታማ የሚያደርጉ፣ ዲጂታላይዜሽንን የሚያፋጥኑ ብቁ ሙያተኞች እንዳሏትም ገለጸዋል፡፡

በመጨረሻም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ደግሞ በየዓመቱ ከተለያዩ የሀገራችን ማዕዘን የመጡ ዜጎች ልምድ እንዲለዋወጡ፣ በተደመረ አቅም ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂና ምርምር ውጤቶችን እንዲያወጡ እያከናወነ ለሚገኘው ስራ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review