የዘጠኝ ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አቀረቡ

You are currently viewing የዘጠኝ ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አቀረቡ

AMN ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የዘጠኝ ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አቅርበዋል ።

በዛሬው ዕለት የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት የአውስትራሊያ ፣ ኩባ ፣አልጄሪያ ፣ ጋምቢያ ፣ ጆርጅያ ፣ ማይናማር ፣ታይላንድ፣ ቬትናም እና ቆጵሮስ አምባሳደሮች ናቸው ።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ እና ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች መታደማቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review