‎የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት የመንግሥት አገልግሎት ዘርፉ ትልቅ ሚና እንዳለዉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing ‎የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት የመንግሥት አገልግሎት ዘርፉ ትልቅ ሚና እንዳለዉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

AMN ሰኔ 03/2017

በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማምጣት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፉ ትልቅ ሚና አለው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት አካሂዷል።

ኮሚቴው በውይይቱ በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የገቡ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና በሁለተኛው ዙር ለመግባት ዝግጅት ያጠናቀቁ ተቋማትን ቅድመ ዝግጅት ተመልክቷል።

በተጨማሪም የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መሶብን ለማስጀመር እያከናወኑ የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴ ሪፖርት ገምግሟል።

በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የገቡ ተቋማት በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

በቀጣይም በሁለተኛ ዙር ወደ መሶብ የሚገቡ ተቋማት እንዲሁም በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ ተግባራት እንዴት መሰራት እንዳለባቸው እና ለተግባራዊ እንቅስቃሴአቸውም ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review