የየካ 2 የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል ለከተማዋ የትራንስፖርት ፍሰት መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላከተ

You are currently viewing የየካ 2 የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል ለከተማዋ የትራንስፖርት ፍሰት መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላከተ

AMN- ግንቦት 13/2017 ዓ.ም

ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ የበቃው የየካ 2 የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል ለከተማዋ የትራንስፖርት ፍሰት መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ተናገሩ፡፡

አስተዳደሩ ከለውጡ በኋላ የከተማዋን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ለማረጋገጥና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለመፍጠር እያደረገ ባለው ጥረት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ያሉት ኃላፊው በዚህም በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለው የትራንስፖርት መሰረተ ልማት የከተማዋን የትራንስፖርት ደህንነት የማሻሻል ዓላማውን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቃው ይህ ተርሚናልም ተጨማሪ አቅም በመፍጠር በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመሙላት የትራንስፖርት ፍሰት እንዲሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

የመኪና ማቆሚያው አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገና በአንድ ጊዜ 1ሺ ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን ለስራው ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና ቀርቧል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review