አገልግሎቱ ያለበትን የሪፎርም ደረጃ ለሚዲያ ባለሙያዎች እያስጎበኘ የሚገኝ ሲሆን፣ የዳታ ቋት ማዕከሉን እና የደንበኞች ጥሪ መቀበያ ስርዓቱን ማሳየት ችሏል።
በዚህም በቀን በአማካኝ እስከ 13 ሺህ ደንበኞችን በ905 የጥሪ ማዕከሉ እያስተናገደና ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ በአገልግሎቱ የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ኃላፊ ወ/ሮ ስምረት በለጠ ገልጸዋል።
ተቋሙ ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት 2017 በጀት ዓመት፣ ከ905 የጥሪ ማዕከል በተጨማሪ ፌስቡክና ቴሌግራምን የመሳሰሉ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መገልገያዎችን ለደንበኞች አገልግሎት እየተጠቀመ እንደሚገኝም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቀጣይ ዓመት “ቁልፍ ደንበኞች” ለሚላቸው ምላሽ መስጫ አዲስ የጥሪ ማዕከል ወደ ስራ ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኑንም ወ/ሮ ስምረት ገልጸዋል።
አገልግሎቱ አዲስ አበባ ካለው ዳታ ማዕከል በተጨማሪ አጋጣሚዎች ቢፈጠሩ ተክቶ መስራት የሚችል ሁለተኛ የዳታ ማዕከል ባህር ዳር ከተማ ላይ እንዳለውም አስታውቋል።