የዴሞክራሲ ባህልን ለማጎልበት የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት ያስገኙ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing የዴሞክራሲ ባህልን ለማጎልበት የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት ያስገኙ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN-ግንቦት ግንቦት 27/2017 ዓ.ም

የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እና የዴሞክራሲ ባህልን ለማጎልበት በመንግስት በኩል የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጣ ያጋጠሙትን መዋቅራዊ ችግሮች እና ፈተናዎች ዘርፈ ብዙ የነበረ መሆኑን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስት፤ በወቅቱ መንግስት የተረከባት ኢትዮጵያ በእዳ የተዘፈቀች፣ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ስራ ያቆሙባት፣የተቋማት ድቀት፣አሳሪ ሕጎች እና ከፋፋይ ትርክት የነገሰባት እንደነበር አንስተዋል።

የመገናኛ ብዙሃን እና የፖለቲካ አውዱ የተበታተነ መሆኑ ነገሮችን ፈታኝ እንዳደረገው ገልጸዋል።

በወቅቱ የነበሩ ከባድ ፈተናዎች መንግስት ጠንካራ እና ፈታኝ ውሳኔዎችን እንዲወስን ማስገደዱን አመልክተዋል።

የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስራ ከነበረበት ሁኔታ ለማስቀጠል ለተቋራጩ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ክፍያ መፈጸሙንና ስራው እንዲቀጥል መደረጉን ነው ያነሱት።

የፖለቲካ አውዱን ለማስፋት እና የዴሞክራሲ ልምምድን ለማጎልበት የተወሰኑ እርምጃዎች ቀላል የሚባሉ እንዳልነበሩ አንስተዋል።

የፖለቲካ እስረኞች መፍታት እና በውጪ የነበሩ ኃይሎችን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት እርምጃ ከዉሳኔዎቹ መካከል የሚጠቀስ እንደነበር አስታውሰዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review