የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

You are currently viewing የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

AMN ሚያዚያ 27 / 2017

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቴሬሴ ካይክዋምባ ዋግነር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቱን በሚያጠናክሩ መስኮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review