በኢትዮጵያ አንጋፋ ከሆኑት አገራዊ ተቋማት መካከል ይጠቀሳል፤ ኢትዮ ቴሌኮም፡፡ በቅርቡ ደግሞ የተቋሙ 10 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ መቅረቡ ይፋ ተደርጓል፡፡ ለረጅም ዓመታት በመንግስት እየተዳደረ ለአገር እና ለሕዝብ ወሳኝ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውን ድርጅት የተወሰነውን ድርሻ ለሕብረተሰቡ እንደሚከፋፈል በዕቅድ ደረጃ መያዙ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተጠቁሞ ነበር፡፡ ዕቅዱ ወደ ትግበራ የሚመጣበትን ጊዜም ብዙዎች ሲጠባበቁት ቆይተዋል፡፡ ጊዜው ደርሶ፣ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቆ፣ ዕቅዱ ለትግበራ ሲደርስ የግዙፉን መንግስታዊ የቴሌኮም ኩባንያ የተወሰነ ድርሻ ወደ ሕብረተሰቡ የማከፋፈሉ ሥራ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. መጀመሩን በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ተደርጓል፡፡
ከሚሰጡት ወሳኝ አገልግሎት በተጨማሪ በአትራፊነታቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት አገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን የኢትዮ- ቴሌኮም የተወሰነ ድርሻ ወደ ኅብረተሰቡ መተላለፉ ዜጎች በአገሪቱ ግዙፍ ኩባንያ ላይ “የእኔ ነው” የሚሉት ድርሻ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በጉዳዩ ላይ በተሰጡ በርካታ ሙያዊ አስተያየቶች ላይ ተንፀባርቋል፡፡ በመንግስት ይፋ በተደረገው የድርሻ ሽያጭ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከድርጅቱ ዳጎስ ያለ ትርፍ ላይ ተቋዳሽ የሚሆኑበትን ዕድልም እንደሚፈጥር ተደጋግሞ ተጠቁሟል፡፡ ለዚህም ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የድርሻ ሽያጩ ይፋ በተደረገበት ዕለት “ኢትዮጵያውያን እጃቸው ላይ የቀረበውን የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻን የመግዛት ዕድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል” የሚል መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

ከምስረታው ጀምሮ 130 ዓመት ገደማ ዕድሜን ያስቆጠረውን፣ በመንግስት ሥርዓት መለዋወጥ ምክንያት የሚከሰቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችን እየተሻገረ አገር እና ሕዝብን በማገልገል የዘለቀውን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገልግሎቱ ስፋት እና ተደራሽነት እያደገ የመጣውን፣ ኢትዮጵያዊ ወሳኝ ተቋምነቱን ከሰፊው አገልግሎቱ ባሻገር “ኢትዮ ቴሌኮም” በሚለው መጠሪያው የሚያንፀባርቀውን ግዙፍ ድርጅት የተወሰነ ድርሻ ለኢትዮጵያውያን የመሸጥ ውሳኔን መነሻ በማድረግ፤ ስለድርጅቱ የረጅም ዓመታት ጉዞ፣ ስኬት እና ተግዳሮት እንዲሁም የ10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ እንደ አገር ያለውን አንድምታ በዚህ ጽሑፍ ለመዳሰስ እንሞክራለን። ለጽሑፉ የሚያግዙ መረጃዎችን ለማግኘት ሰነዶችን እና የኩባንያውን ገፀ ድር ተመልክተናል፤ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አስተያየትም አክለናል፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍ ትናንት
አሁን ላይ “ኢትዮ ቴሌኮም” በመባል የሚጠራው ግዙፍ ኩባንያ ውልደቱ በ1886 ዓ.ም. እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ። በኢትዮ ቴሌኮም ይፋዊ ገፀ ድር ቋት ውስጥ “የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍ አመሠራረት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የተቀመጠው መረጃም ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡ እንደመረጃው ከሆነ፤ የአገልግሎቱ መጀመር ዕውን የሆነው ከሐረር ከተማ ወደ አገሪቷ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የ477 ኪሎ ሜትር የቴሌፎንና ቴሌግራፍ መስመር በተዘረጋበት ጊዜ ነበር፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግም ከአዲስ አበባ በሁሉም አቅጣጫዎች ወደሚገኙ የአገሪቷ አካባቢዎች የመገናኛ መስመሮች እየተስፋፉ ሄዱ። በርካታ የአገሪቷ ዋና ዋና ከተሞች በኦፕሬተሮች አማካኝነት የቴሌኮሙኒኬሽን መገናኛ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን በቁ፡፡ በየከተሞቹ በተቋቋሙ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች አማካኝነት በሩቅ ቦታ የሚኖር ፈላጊና ተፈላጊ በስልክ የሚገናኙበት ዕድል በስፋት መፈጠር ቻለ፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ ተቋም በየዘመናቱ የተለያዩ መጠሪያ ስያሜዎችን እና መዋቅራዊ አደረጃጀቶችን በመያዝ ተቋማዊ ጉዞ አድርጓል፡፡ ለማሳያነት ያህል ከ1886 እስከ 1934 በነበሩት ዓመታት ውስጥ ተቋሙ በተለያዩ ስያሜዎችና መዋቅሮች ሲጠራና ሲሠራ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቱን መስጠት በጀመረበት ወቅት፤ በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ- መንግስት አስተዳደር ሥር ሆኖ “የኢትዮጵያ የቴሌፎንና የቴሌግራፍ ማዕከላዊ አስተዳደር” በሚል ስያሜ ይጠራ ነበር፡፡ በዚህ መጠሪያ ከ1886 እስከ 1900 ዓ.ም. ድረስ ሲሠራ ቆይቷል። የተቋሙ የወቅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ሚስተር ስቴቨኒን የተባሉ ፈረንሳዊ ዜጋ ነበሩ፡፡ ከ1900–1903 ዓ.ም.ድረስ “የኢትዮጵያ የፖስታ፣ ቴሌግራፍ እና ቴሌፎን ማዕከላዊ ቢሮ” የሚል የስያሜ ለውጥ ተደርጎለት የስዊስ አገር ዜጋ በነበረው የዳግማዊ ምኒልክ አማካሪ አልፍሬድ ኢልግ እየተመራ አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል። በ1903 ዓ.ም. የቀደመ ስያሜውን “የፖስታ፣ የቴሌግራፍ እና ቴሌፎን ሚኒስቴር (ፖቴቴ)” ወደሚል በመለወጥ፤ ሚስተር ሊዮ ሸፍኖ በተባለ የፈረንሳይ ዜጋ እየተመራ አገልግሎቱን መስጠት ችሏል፡፡ በሂደት ተቋሙን የመምራት አቅምና ብቃት ማዳበር የቻሉት ኢትዮጵያውያን የውጭ አገር አመራሮችን ቦታ መያዝ ቻሉ። በዚሁ መሰረት ከሚስተር ሊዮ ሸፍኖ በኋላ እነልጅ ግዛው በዛብህ፣ እነልጅ በየነ ይመር እና በመሳሰሉት ለመተዳደር በቃ፡፡
የጣሊያን ወራሪ ኃይል የኢትዮጵያን ምድር ረግጦ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥ እንደ አገር ከደረሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንዱ መሰረታቸውን ያፀኑ አገር በቀል ተቋማት እንዲዳከሙ ማድረጉ ነው፡፡ ብዙ የተደከመበት የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተቋምም በወረራው ወቅት ተግዳሮቱ ደርሶበታል፡፡ ኢትዮጵያ ወራሪውን አሸንፋ ነፃነቷን እንደተቀዳጀት በተቋማቶቿ ላይ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን ፈጥና ከውናለች። በዚሁ መሰረት “የፖስታ፣ ቴሌግራፍና ቴሌፎን ሚኒስቴር” ተቋቁሞ የቴሌፎን፣ የቴሌግራፍና የሬዲዮ መገናኛዎችን የማስተዳደር ተግባር ተረክቦ እንዲሠራ ኃላፊነት ተሰጠው፡፡ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱም በወቅቱ በመላ አገሪቷ የመገናኛ ኔትዎርኩን እንደገና የማቋቋም፣ የረጅም መስመር መገናኛዎችን የመጠገን ሥራ ላይ በዋናነት በማተኮር አከናውኗል።
አንጋፋው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ ተቋም፤ በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥት “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ቴሌኮሙኒኬሽን ቦርድ (Imperial Board of Telecommunication of Ethiopia – IBTE)” በሚል ስያሜ በአዋጅ ቁጥር 131/45 በመቋቋም ከጥቅምት 5 ቀን 1945 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠቱን ቀጠለ፡፡ በተመሳሳይ፤ በደርግ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን በተለያዩ ስያሜዎች በመጠራት አገልግሎቱን ሰጥቷል፡፡ ተቋሙ ከጥቅምት ወር 1967 ዓ.ም. እስከ ጥር ወር 1973 ዓ.ም.ድረስ የሶሻሊስት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ድርጅት እንዲሁም፤ ከጥር ወር 1973 እስከ 1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በሚሉ ስያሜዎች ሲጠራ ቆይቷል። በእነዚህ ጊዜያት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከአውቶማቲክ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ለውጥ መደረጉን የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ያመለክታል፡፡
ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በተመሰረተው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አማካኝነት የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉ በአዲስ መልክ እንደገና እንዲዋቀር ተደርጓል። በዚህ ወቅት የተሠራው መዋቅር ሁለት የተለያዩና ራሳቸውን የቻሉ ተቋማት ማለትም የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ (ሬጉላቶሪ አካል) እና የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን (ኦፕሬተር አካል) በአዋጅ ቁጥር 49/1989 መሠረት እንዲቋቋሙ ምክንያት ሆኗል፡፡ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለአገራችን ልማት ያለው አበርክቶ እንዲጎለብት እና በቀጣይ ዕድገት የሚጫወተው ቁልፍ ሚና እንዲጠናከር በመታሰቡ ኢትዮ ቴሌኮም ሕዳር 20 ቀን 2003 ዓ.ም እንዲመሠረት አድርጓል።
ኢትዮ ቴሌኮም አሁን
ኩባንያው በአሁኑ ሰዓት በብዙ መመዘኛ ውጤታማ የሆኑ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ ተቋሙ በቅርቡ በይፋዊ ገፀ ድሩ ያሰፈረው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ የአገልግሎት ተደራሽነቱ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል፡፡ አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥር 80 ሚሊዮን ገደማ ደርሷል፡፡ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ብዛት ደግሞ ከ75 ሚሊዮን በላይ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡ ከ40 ሚሊዮን የሚበልጡ ደንበኞቹ የኢንተርኔት አገልግሎት እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ሦስት ዓመታትን ብቻ ባስቆጠረው የቴሌ ብር የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የሚገለገሉ ደንበኞቹን ቁጥር 47 ነጥብ 55 ሚሊዮን አድርሷል፡፡ ለዚህ ስኬት ባለፉት ስድስት ዓመታት የተከናወኑት ወሳኝ ሥራዎች መሠረታዊ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ ጥቂት ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን መገንባት ተችሏል። ከብዙ ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነቶችን በመመሥረት የቴሌኮም ሥነ ምኅዳሩ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያስመዘግብ አድርጎታል። በዘርፉም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ ጀማሪ ቢዝነሶችን መደገፍና በሌሎችም ጉዳዮች ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አድርጎታል፡፡
ዘርፈ ብዙ ዕድገት እያሳየ የመጣው ኢትዮ ቴሌኮም ገቢው እና አትራፊነቱ ከዓመት ዓመት ከፍ እያለ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ በዚህ ዘርፍ ያለውን የኩባንያውን ዕድገት ለመረዳት ያክል የ2014 እና የ2016 በጀት ዓመታት ገቢውን በንፅፅር እንመልከት። ከኩባንያው በተገኘ መረጃ መሠረት፣ በ2014 በጀትዓመት መጨረሻ ያገኘው አጠቃላይ ገቢ 61 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፤ በ2016 የበጀት ዓመት ይህ ገቢ 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በቴሌ ብር አገልግሎት አማካኝነት ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ ዝውውር እንዲከናወን አስችሏል፡፡ ኩባንያው የቴሌ ብር አገልግሎትን በይፋ ከጀመረበት ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አጠቃላይ 2 ነጥብ 55 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ዝውውር ማሳለጥ ችሏል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ ከገቢው አንጻር ከተመለከትን ከዓመት ዓመት ዕድገት እያሳየ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በየዓመቱ የወጡ የኩባንያውን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት መነሻ አድርገን ከ2011 እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ ያሳካውን የገቢ መጠን ብንመለከት በፈጣን የዕድገት ጎዳና እየተጓዘ መሆኑን እንረዳለን። በየዓመቱ ይፋ የሆኑ የኩባንያው የገቢ አፈፃፀም ሪፖርት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ በ2011 በጀት ዓመት በአማካይ ከ40 እስከ 50 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ በማድረግ 36 ነ 3 2012 477 1051 ጥብ 3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቷል፡፡ በ2012 በጀት ዓመት ደግሞ፤ ኩባንያው 47 ነ?? 7 105 1 ጥብ 7 ቢሊዮን ብ? 105 1 ር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የዕቅዱን 105 ነ 1ጥብ 1 ከመቶ በ31 4 ማሳካት የላቀ አፈጻጸም አስመዝግቧል፤ ይህ ውጤት ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ31 ነጥብ 4 ከመቶ አድጓል።ኩባንያው በ2013 በጀት ዓመት 56 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የዕቅዱን 101 ነጥብ 7 ከመቶ አሳክቷል። ይህ ገቢ ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ18 ነጥብ 4 ብልጫ እንደነበረው ሪፖርቱ አመላክቷል።
በተመሳሳይ በ2014 በጀት ዓመትም ኢትዮ ቴሌኮም በገቢ ደረጃ ውጤታማ የሚባል ጊዜን አሳልፏል፡፡ የበጀት ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እንደጠቆመው፤ በበጀት ዓመቱ 61 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብ? 876 20143 4732013 85
?2015 2016 ር አጠቃላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን፤ አፈፃፀሙ የዕቅዱን 87 ነ?? 62014 3 4732013 8 52015 ?2016 ነጥብ 6 ከመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኩባንያው በ2014 በጀት ዓመት ከዕቅዱ አንፃር ዝቅ ያለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል፡- በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተለይም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በእነዚህ ምክንያት 3 ሺህ 473 የሞባይል ዕጣ 2013 85?2015 2016 ቢያዎች አ201385
?2015 ?2016 ገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ከታቀደው የገቢ እቅድ አኳያ ክፍተት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ የበጀት ዓመቱ ገቢ ከ2013 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ8 ነጥብ 5 ከመቶ ዕጣ 2015 2016 ድገት አምጥቷል፡፡
የ2015 እና የ2016 በጀት ዓመታት የኢትዮ ቴሌኮም ገቢ አፈፃፀም በውጤታማነቱ የቀጠለ ነበር። በ2015 በጀት ዓመት ኩባንያው የገቢ ምንጮችን በማስፋት በዋናነት ከመሠረታዊ ቴሌኮም አገልግሎቶች ባሻገር ያሉ በርካታ ተቋማትና አጠቃላይ ደንበኞችን ማዕከል ያደረጉ የዲጂታል መፍትሔዎች፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እንዲሁም የኔትዎርክና የሲስተም አቅም በማሳደግ 75 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የዕቅዱን 101 ከመቶ አ ?2352016 20158 9 783 937 2015 21 7?167 ሳክቷል፡፡ ይህ ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ23 ነጥብ 5 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ ለኩባንያው የ2016 በጀት ዓመት መሪ የሦስት ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ ሁለተኛ ዓመት ያጠናቀቀበት ነበር፡፡ በውጤቱም የቴሌኮም ደንበኞቹን ቁጥር ከ2015 ተመሳሳይ ወቅት በ8 ነጥብ 9 ከመቶ በማሳደግ 78 ነጥብ 3 ሚሊዮን አድርሷል፡፡ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢውንም ወደ 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ከፍ አድርጓል፡፡ ይህም ከ2015 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ21 ነጥብ 7 ከመቶ ወይም በ16 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ያሳየ ሆኗል፡፡
አስር ከመቶ ድርሻው ለሽያጭ የመቅረቡ ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳ
የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ሽያጭ በይፋ በተጀመረበት ዕለት መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደጠቆሙት፤ የኢትዮ ቴሌኮም የሀብት መጠን 100 ቢሊየን ብር ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ ለሽያጭ የቀረበው 10 በመቶው ነው። በዚሁ መሰረት ኢትዮ-ቴሌኮም ለሽያጭ ያቀረበው አጠቃላይ አክሲዮን ብዛት ዋጋ 100 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ለሽያጭ የቀረበው የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈጻሚዋ፣ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው ሼር 33 መሆኑን እና በብር ሲተመን 9 ሺህ 900 ብር መሆኑ ተጠቁሟል። የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌ ብር መተግበሪያ አማካኝነት እየተከወነ ይገኛል፡፡ እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የአክሲዮን ሽያጭ እና ግዢው እንደሚቆይ የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት ሲሆን፤ ኢትዮ ቴሌኮም ለሽያጭ ያወጣው የአክሲዮን መጠን ቀድሞ ከሞላ ቀኑ ሳይድርስ ሊያቆም እንደሚችል ተጠቁሟል።
ይህንን መነሻ በማድረግ ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳው ምን ይመስላል? በሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ላይ ሃሳባቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ቆስጠንጢኖስ በርኸ ናቸው፡፡ እሳቸውም በምላሻቸው እንደጠቆሙት፤ እንደ አገር የካፒታል ገበያ ስርዓትን ለማስፋፋት በመንግስት ደረጃ ቀደም ብሎ የተያዘ ሃሳብ እና ዕቅድ ነው፡፡ ዕቅዱን ወደ ተግባር ለመቀየር ጥናት ላይ የተመሰረተ ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ተግባራዊ እንቅስቃሴው የመንግስት ተቋማት ከሆኑት መካከል እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉትን የተወሰነ ድርሻ ለዜጎች በማስተላለፍ መከናወኑ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው፡፡ ይህ ጅምር ዕውን መሆኑ እንደ አገር በርካታ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በመንግስት ብቻ በተያዙ ሴክተሮች የግል ድርጅቶች እና ሕብረተሰቡ የተወሰነውን ድርሻ ወስዶ የሚሳተፍበት ሁኔታ መፈጠሩ፤ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ ጥራትን ለማሻሻል፣ የባለቤትነት ስሜት በብዙሃኑ ላይ ለመፍጠር ያግዛል፡፡
“የኢትዮ ቴሌኮም የተወሰነ ድርሻ ለኢትዮጵያውያን ለማስተላለፍ ይፋ የተደረገው እና ወደ ትግበራ የተገባው መንግስታዊ ውሳኔ በጥናት ላይ ተመስርቶ በጥንቃቄ የተሠራ ስለመሆኑ የድርሻ ሽያጩን አስመልክቶ የወጡት መስፈርቶች ያመላክታሉ” ያሉት የምጣኔ ሃብት ምሁሩ፤ ከዚህም መንግስት እና ሕብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ዕድል ስለመኖሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም ሲያብራሩ፤ “ግዙፍ ከሆኑ መንግስታዊ ተቋማት ከሚሸጠው ድርሻ ቀላል የማይባል ገንዘብ ይሰበሰባል፡፡ ይህን ገንዘብ ደግሞ መንግስት እጅግ አስፈላጊ እና ወሳኝ ለሚላቸው ሌሎች ተግባራት ማስፈፀሚያ ያውለዋል፡፡ ይፋ የተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ መስፈርት አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሊያሳትፍ የሚችል ነው፡፡ ኩባንያው እያስመዘገበ ያለው ዕድገት እና የአትራፊነት ደረጃን ስንመለከት ደግሞ፤ አንድ ኢትዮጵያዊ ገንዘቡን በባንኮች አስቀምጦ ከሚያገኘው ወለድ ብልጫ ያለውን ትርፍ ማግኘት የሚችልበትን ዕድል ለዜጎች የሚያቋድስ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ከተመለከትነው፤ ይህ ጅምር ለካፒታል ገበያ ስርዓት አዲስ የሆነው ሕብረተሰብ በዘርፉ ውስጥ በስፋት እንዲገባና በተግባር የተደገፈ ልምምድ እንዲያደርግ ምቹ ምህዳር ይፈጥርለታል” ብለዋል፡፡
እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉትን በመንግስት ብቻ ሲተዳደሩ የነበሩ ኩባንያዎችን የተወሰነ ድርሻ ወደ ሕብረተሰቡ እና የግል ባለሃብቶች የማስተላለፉ የካፒታል ገበያ ሥርዓት በኢትዮጵያ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ እመርታ ሊያመጣ እንደሚችል ቆስጠንጢኖስ (ዶ/ር) ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እሳቸው እንዳብራሩት፤ የካፒታል ገበያ ሥርዓት እንደ አሜሪካ እና አውሮፓ ባሉ የበለጸጉ አህጉራት ውስጥ የሚገኙ አገራት ብቻ ሳይሆን እንደ ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ እና መሰል የአፍሪካ አገራትም በስፋት የሚተገበር ነው። ጎረቤታችን ኬንያን ብንመለከት የካፒታል ገበያ እንቅስቃሴዋ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን መስክ በስፋት ልትተገብረው ይገባል፡፡ የካፒታል ገበያው በሂደት ለውጭ አገራት ኩባንያዎች እና ዜጎች ክፍት የሚሆንበት አሠራር ውስጥ መገባት ይኖርበታል። ምክንያቱም የውጭ አገራት ኩባንያዎች እና ዜጎች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ውስጥ መሳተፍ ከቻሉ፤ አገሪቷ በሌሎች አገራት ያሉትን የተለያዩ አቅሞችን (ለምሳሌ የውጭ ምንዛሬ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂ፣ ዕውቀት፣ የአሠራር ስርዓት…) በቀላሉ ታገኝበታለች፡፡ አገር በቀል ኩባንያዎች ዕድገታቸው እና ውጤታማነታቸው ይፋጠናል፤ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውም ያድጋል፡፡
በኢትዮ ቴሌኮም እየተተገበረ ያለው የድርሻ ሽያጭ ጅምር በቀጣይ እንደ አገር ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲከወን በመንግስት፣ በሕብረተሰቡ እና በተቋማት ደረጃ የሚጠበቁ ሃላፊነቶችን ጠቅሰው ምክረ ሃሳባቸውን እንደሚከተለው አጋርተዋል። መንግስት የካፒታል ገበያን ውጤታማ ለማድረግ በአሠራር ስርዓቱ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጥናት ላይ በመመስረት መፍትሄ መስጠት ይገባል። ዘርፉን ውጤታማ እና ስኬታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ሕግ እና መመሪያዎችን ማውጣት፣ እንዲተገበሩ ማድረግ እንዲሁም ሥራን የሚያስተጓጉል ሳይሆን የሚያቀላጥፍ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የካፒታል ግብይቱን የሚያከናውኑ ተቋማት አቅማቸውን በሁሉም መስክ በማጎልበት ሥራቸውን በአግባቡ መከወንና ሃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፡፡ ሕብረተሰቡ በካፒታል ገበያ ሥርዓት ውስጥ በንቃት መሳተፍ አለበት፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ጥናትን መሰረት ባላደረጉ አስተያየቶች መደናገር አያስፈልግም። መንግስት ወደዚህ ተግባር የገባው ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ እና አስቦበት መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ያለውን የዕውቀት እና የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት የዘርፉ ሙያተኞች፣ የሠራተኛ ማህበራት፣ የአሠሪዎች ፌዴሬሽን፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት … ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጊዜ ሂደት ትውልዱ የሚማርበትን፣ ከዘርፉ የሚላመድበትን በአግባቡ የሚተገበርበትን መሰረት መፍጠር ከሁሉም ይጠበቃል፡፡ ይህ ከሆነ፤ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሥርዓቱ ውጤታማ መሆን ይችላል፡፡
በደረጀ ታደሰ