የጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

You are currently viewing የጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

AMN-የካቲት 21/2017 ዓ.ም

ከትናንት በስትያ የጀመረው የኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ምስረታ ሚንስትሮች መድረክ የጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።

መድረኩ በቴክኒካል ኮሚቴው አማካኝነት ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ሲያደርግም ቆይቷል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ለመመስረት የሚያስችል ጉዳዮች ላይ በጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ሰፊ ውይይት ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል።

የኮሪደሩ መመስረት በኮሪደሩ ተሳታፊ አገሮች መካከል የመሰረተ-ልማት ትስስር በመፍጠር፣ ትብብርን በማስፋፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን በማጎልበት ክልላዊ ውህደትን ለማጠናከር የሚረዳ እንደሚሆን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review