AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም
የጅቡቲ መንግስት በሀገሪቷ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት መስሪያ የአራት ሄክታር መሬት በስጦታ አበርክቷል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የመሬት ስጦታው ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ያላቸውን መልካም ወዳጅነት ማሳያ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በመስሪያ ቦታው ላይ በቅድሚያ የመዋለ−ህጻናት ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የገቢ ማሰባሰብ እና በስራ ሂደቱ ላይ ከኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝም አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጠቁመዋል።