የገቢዎች ሚኒስቴር ከአይ.ኤም.ኤፍ የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክ እርዳታ ማዕከል ጋር ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገለጸ

You are currently viewing የገቢዎች ሚኒስቴር ከአይ.ኤም.ኤፍ የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክ እርዳታ ማዕከል ጋር ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገለጸ

AMN – ጥር 21/2017 ዓ.ም

የገቢዎች ሚኒስቴር ከአይ. ኤም. ኤፍ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የቴክኒክ እርዳታ ማዕከል ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱም የገቢውን ዘርፍ የመምራት ኃላፊነት ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ታደሰ ገልፀዋል።

ከነዚህም መካከል ለደንበኞች የላቀ አገልግሎት መስጠትን ዓላማ ያደረገው በቴክኖሎጂ የታገዘ የደንበኞች አገልግሎት ቀዳሚው መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህንን ራዕይ ለማሳካትም እንደ አይ.ኤም.ኤፍ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የቴክኒክ እርዳታ ማዕከል የመሳሰሉት ድርጅቶች ትልቅ ሚና እንዳላቸውና ሚኒስቴሩም አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የስትራቴጂክ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዑስማን መሐመድ በበኩላቸው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደ አውሮፓ ህብረት፣ ቲቢአይ፣ ቢኤምጂኤፍ እና የመሳሰሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

የአይ ኤም ኤፍ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የቴክኒክ እርዳታ ማዕከል በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ ልምድ ካላቸው ግዙፍ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከእንዲህ ዓይነቱ ድርጅት ጋር ተባብሮ መስራት ለሚኒስቴሩ ተጨማሪ እድል የሚከፍት እንደሆነም አንስተዋል።

የአይ ኤም ኤፍ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የቴክኒክ እርዳታ ማዕከል ተወካዮች በበኩላቸው፣ የድርጅቱ ዋና ዓላማ ለሚኒስቴሩ የቴክኒክ እርዳታ እና የአቅም ግንባታ መስጠት መሆኑን ገልፀው፣ ለዚህም የሚኒስቴሩን ድጋፍ መጠየቃቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review