AMN – ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም
“380 ሄክታር የሚሸፍነውና በሶማሌ ክልል የሚገኘው የገበታ ለሀገር ሥራ አንዱ አካል የሆነው የሸበሌ ፕሮጀክት ለወደፊት የመስፋፋት ከፍተኛ አቅም አለው።“ ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የትኛውንም የሀገራችን ጫፍ ስንጎበኝ ኁልቆ መሳፍርት ከሌላቸው እድሎች እና ተስፋዎች ጋር እንገናኛለን“ ብለዋል፡፡
“ኢትዮጵያ እያንሰራራች ነው። በፈተናዎች ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች በሚታዩ አስደናቂ እድገቶች ከፍ እያለች ትገኛለች። የጋራ እድገታችን ለዘላቂ ልማት እና ብልጽግና መሠረት የሆነውን ሰላምን በመጠበቅ ላይ የተመሠረተ ነው።
ለትውልድ ሁሉ የፈካ መፃዒ እድል ሰላማችንን እንጠብቅ።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስት ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡