የግብርናው ዘርፍ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለኤክስፖርት አስታወጽኦ አበርክቷል – ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)

You are currently viewing የግብርናው ዘርፍ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለኤክስፖርት አስታወጽኦ አበርክቷል – ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 5/2017

የግብርናው ዘርፍ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለኤክስፖርት አስታወጽኦ ማበርከቱን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለጹ።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) የዘርፎች አፈጻጸምን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በግብርና ዘርፍ ዘንድሮ ከታቀደው 8 ነጥብ 4 በመቶ አጠቃላይ እድገት ውስጥ 6 ነጥብ 1 በመቶ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ግብ መጣሉን ገልጸዋል።

ባለፈው የመኸር ወቅት 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን እና ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ3 ሚሊዮን ሄክታር ብልጫ እንዳለው ጠቅሰዋል።

ይህም በስንዴ ምርት ብቻ ሲታይ ዘንድሮ 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መመረቱን ገልጸው፤ የግብርና ዘርፉ ለአጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመላክተዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የግብርናው ዘርፍ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለኤክስፖርት አስታወጽኦ ማበርከቱን አንስተው አፈጻጸሙ ከእቅዱ የ19 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ነው የገለጹት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review