የግብርና ሚኒስቴር ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የእንስሳት ጤና አገልግሎት መስጫ ግብአቶችን ለክልሎች አስረከበ

You are currently viewing የግብርና ሚኒስቴር ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የእንስሳት ጤና አገልግሎት መስጫ ግብአቶችን ለክልሎች አስረከበ

AMN – ሚያዚያ 24/2017

የግብርና ሚኒስቴር በአርብቶ አደሮች ኑሮ ማሻሻያ ላይ ከሚሰሩ ፕሮጀክቶች ጋር በመተባበር ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የእንስሳት ጤና አገልግሎት መስጫ ግብአቶችን ለክልሎች አስረክቧል።

በመድረኩ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴን (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችና የላብራቶሪ እቃዎችን አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ለሚገኙባቸው ኦሮሚያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልሎች አስረክበዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ግብርናውን ለማሻሻል ከሚሰሩ ስራዎች መካከል በአርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ እንስሳትን እና የእንስሳት ተዋፅኦ ውጤቶችን ማዘመን ይገኝበታል።

አርብቶ አደሩንና ከፊል አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ውጤታማ የሆኑ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ለአርሶ አደሮቹ የተሰጡት ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ክሊኒክና ሌሎች ግብዓቶች ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የስጋ ጥራት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ ከቁም እንስሳት እና የእንስሳት ተዋፅኦ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ የተሻለ እንዲሆን ያግዛል ነው ያሉት።

ከዚህ በፊት ለአፋርና ሶማሌ ክልሎች ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ክሊኒኮች እና የላብራቶሪ እቃዎች መከፋፈሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review