የግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ የንግዱ ማህበረሰብ የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing የግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ የንግዱ ማህበረሰብ የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

AMN-ግንቦት 16/2017 ዓ.ም

የግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ የንግዱ ማህበረሰብ የሚያነሷቸዉን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባዘጋጀዉ የዉይይት መድረክ ላይ የተገኙት፤ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ፤የንግዱ ማህበረሰብ ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የመልካም አስተዳደር ችግር ተጠቃሽ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ከሌብነት እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ የንግዱ ማህበረሰብ የሚያነሷቸዉ ችግሮች በተጨባጭ የሚታዩ እንደሆነ ገልፀዉ፤ ይህንንም ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አንስተዋል።

የሀገርን እና የመንግስትን ገፅታ የሚያበላሹ መሰል ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ፤ የተቀናጀ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዳበር እና ቴክኖሎጂ ላይ መሰረት ያደረጉ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

በትባረክ ኢሳያስ

See insights and ads

Boost post

All reactions:

7878

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review