AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር በመሆን የጎንደር የኮሪደር ልማት እና የፋሲለደስ ግንብ እድሳት የደረሰበትን ደረጃ መጎብኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
ከንቲባዋ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ እና የፋሲለደስ እድሳት እጅግ በጣም ውብ፣ የከተማዋን ታሪካዊነት ይበልጥ በሚያጎላ እና የቱሪስት መዳረሻነቷን በሚያሳድግ ሁኔታ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።
በዚህ የለውጥ ዘመን የኢትዮጵያ ከተሞች የተሰጣቸው ትኩረት እጅግ ትልቅ መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ በተለይም ለነዋሪዎች ምቹ እና ውብ እንዲሁም ለቱሪስት መስህብ መሆናቸውን እጅግ የሚጨምር ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።