AMN-የካቲት 19/2017 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ምልከታ አድርገዋል፡፡
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተቋሙ የበለፀጉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቴክኖሎጂ ስራዎችን መገምገሙንና በኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱን ስራዎች በተመለከተ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ዝርዝር ማብራሪያ ማቅረባቸውም ተገልጿል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከዕድሜው በላይ የሆኑ ስራዎች መስራቱን የሱፐርቪዥን ቡድኑ መሪ ቀነዓ ያደታ(ዶ/ር) አንስተው፣ ተቋሙ ለሀገር ትልቅ አቅም እንደሆነ መጠቆማቸውም ተመላክቷል፡፡
ይህን አቅም በተለያዩ ዘርፎች ለሚታዩ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅርበት መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ በበለፀጉ የቴክኖሎጂ ስራዎች የብዙኃንን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት ስለሚሰራበት አግባብ በሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት ጥያቄዎች ቀርበው በዋና ዳይሬክተሩ ምላሽ እንደተሰጣቸውም ከኢንስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡