የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

You are currently viewing የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

AMN – ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

አመራሮቹ የካዛንችስ ኮሪደር ልማትን የገላን ጉራ የመኖሪያ መንደርን የአዲስ አለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል እና የጫካ ፕሮጀክትን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ወይዘሮ አለምፀሀይ ጻዉሎስ፤ ጉብኝቱ በትብብር ሀገራዊ ስኬትን ማስመዝገብ እንደሚቻል ግንዛቤን የሚፈጥር የልማቶቹን ፋይዳ ተገንዝቦ ለቀጣይ ስኬት መነሻ እንዲሆን እድልን የሚፈጥር ነዉ ብለዋል፡፡

በመዲናዋ የተሰሩ እና የሚሰሩ ልማቶት ሰዉን ማዕከል ያደረጉ እርስ በዕርስ የተሳሰሩ በሁለንተናዊ መልኩ ሀገርን የሚጠቅሙ ሆነው የተሰሩ ስለመሆናቸውም ተብራርቷል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review