የጥምቀት በዐል ሀይማኖታዊ ትዉፊቱን በጠበቀ መልኩ ለማክበር የሚያስችለው የሰላም ሰራዊት አባላት ዉይይት ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነዉ

May be an image of text

AMN-ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የጥምቀት በዐል ሀይማኖታዊ ትዉፊቱን ባስጠበቀ እና ሀገራዊ ገፅታን በሚያጎላ መልኩ ለማክበር የሰላም ሰራዊት አመራር እና አባላት የዉይይት እና የስምሪት ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሊድያ ግርማ አዲስ አበባ ሰላም የሰፈነባት እና የተረጋገጠባት እንድትሆን የፀጥታ ሀይሎች እና የመዲናዋ ነዋሪዎች ቅንጅታዊ ስራ የጎላ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡

በመዲናዋ አስተማማኝ ሰላም መስፈኑ የሚጀመሩ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት እና በጥራት እንዲጠናቀቁ እያደረገ ነውይህም ከተማዋን የአለም የትኩረት ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ቀናት የሚከበሩት የከተራ እና የጥምቀት በዐላትም በድምቀት ይከበሩ ዘንድ የፀጥታ አካላት ከሰላም ሰራዊት አባላትና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ይሰራሉ ተብሏል፡፡

በተመስገን ይመር

All reactions:

3030

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review