AMN – የካቲት 28/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት ካውንስል “መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ እና ከነገ ወዲያ በመስቀል አደባባይ መንፈሳዊ መርሐ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ካውንስሉ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
በመግለጫውም ከ1 ሺህ 600 በላይ አብያተ−ክርስቲያናት ከቢል ግራሃም የወንጌል ማኅበር ጋር በመተባበር፤ በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው መንፈሳዊ መርሐ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የቄስ ቢሊ ግራሃም ልጅ ፍራንክሊን ግራሃም መጋበዛቸው ተጠቁሟል።
ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጵያ ትልቅ አክብሮት እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ባለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸውም ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና አቅራቢያዋ የሚገኙ ክርስቲያኖች የካቲት 29 እና 30 2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በመገኘት በዚህ የጸሎት፣ የወንጌል እና የምስጋና ድግስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመሀመድኑር አሊ